ዶ/ር መኩሪያ ሀይሌ

ዶ/ር መኩሪያ ሀይሌ

  • ኮሚሽነር Since Jun 21 2021
  • ይፋዊ ምስል ማውረድ

ዶ/ር መኩሪያ ሀይሌ  ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ ማኔጅመንት የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው እና በአየርላንድ እና እንግሊዝ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በዓለም አቀፍ ቢዝነስ ማኔጅመንት እና ቢዝነስ አስተዳደር ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን ሶስተኛ ዲግሪያቸውን ደግም ... 2020 ከኮሪያ ከፍተኛ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (KAIST) ደቡብ ኮሪያ ዩኒቨርሲቲ የኢንፎርሜሽን እና ቴሌኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ማኔጅመንት 2020 ዶክትሬታቸውን ይዘዋል፡፡

 

የተከበሩ መኩሪያ ኃይሌ(/) የኢትዮጵያ ከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በፐብሊክ ሴክተር የመጀመርያ ስራ የሰሩት የደቡብ ክልል ንግድ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ እና የደቡብ ክልል ካቢኔ አባል ነበሩ። ከዚያም ወደ ኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተዛወሩ።

ዶክተር መኩሪያ 1992 ጀምሮ በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን አሁን ላይ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንን በሀላፊነት በመምራት ላይ ይገኛሉ

የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በአዲስ መንፈስ የተነቃቃ እና አገልጋይነትን የተላበሰ ሲቪል ሰርቫንትን  በመፍጠር በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ስርዓትን ለመቀየር ተግባራዊ እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡

ኮሚሽኑ ቀጣይነት ባለው መልኩ የሲቪል ሰርቪስ ስርዓቱን ለመቀየር የሚያስችሉ ተግባራትን በማከናወን ውጤታማ መሆን ይጠበቅበታል፡፡

ለዚህም ቀልጣፋ የተቋማት አደረጃጀት እና የስራ ምዘና ስርዓት መዘርጋት፣ የሰው ሀብት ብቃት ስራ አመራር ስርዓትን መተግበር እና የአፈፃፀም ስራ አመራር ስርዓትን መተግበር ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራቸው ተግባራት ይሆናሉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያን በመተግበር ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት እንዲኖር ማድረግና የኤሊክትሮኒክስ ገቨርንመት (E-Governmnet) ስርዓትን መዘርጋት ይጠበቅበታል፡፡

የለውጥ አመራር ስርዓትን በሀገራችን የሲቪል ሰርቪስ ስርዓት ግንባታ ቀጣይነት የሚያረጋግጥና ህሊናዊና ተጨባጭ ነባራዊ ሁኔታ በሚያጣጥም መልኩ ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራባቸው ጉዳዮች ይሆናሉ፡፡

ለሀገራችን ኢትዮጵያ መለወጥ ብሎም እንደ ዘርፍ ለሲቪል ሰርቨሱ ስርዓት መቀየር የሁላችንም ርብርብ እና ሚና ወሳኝ መሆኑ ገልጽ ነው፡፡ ለዚህም  በተባበርና በአንድ መንፈስ የሲቪል ሰርቪሱን ስርዓት ለመለወጥ እንድንተጋ ጥሪዮን አቀርባለሁ፡፡

 

መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር)

የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር