ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም. የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የአዲሱ ትውልድ ሲቪል ሰርቪስ ግንባታ ፖሊሲ ማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎች እና አገራዊ የተገልጋዮች እርካታ ጥናት ሪፖርት ላይ ወርክ ሾፕ አካሄደ

በወርክ ሾፑ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ሀይሌ ሲሆኑ በንግግራቸውም የአዲሱ ትውልድ ሲቪል ሰርቪስ ግንባታ ፖሊሲ ማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎች አሁን ካለንበት አጠቃላይ አገራዊ ሁኔታ እንደ ካስማ የሚያገለግል ነው። በመሆኑም ሲቪል ሰርቪሱ አሁን ካለበት ችግር እንዴት ሊወጣ እንደሚችል ቢያንስ በፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች አስቀምጠን መስመሩን ከለየን የሚቀጠለው ትውልድ መስመሩን ተከትሎ ሊያስተካክለው እንደሚችል ገልፀዋል፡፡

ልክ እንደ አገራችን የሽመና ውጤት የባህል ልብሳችን ስትለፋ ስትደክም አመርቂ ውጤት እንደሚያስገኝው ሁሉ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የእውነት እነዚህ ፖሊሲዎች መሬት ላይ ተግባረዊ ካደረጋቸው በእርግጠኝነት የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ግንባታ ልክ እንደ ጥበብ ልብስ ሰሪዎች ውጤቱ ያማረ እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡

ለዚህም መሳካት ሁሉም አብሮ ተባብሮ መስራት እንደሚኖርበት እና እነዚህ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች አዲሱ መንግስታዊ መዋቅር ካለቀ በኃላ ተግባራዊ እንደሚደረግ ኮሚሽነሩ አመላክተዋል፡፡

በወርክ ሾፑም ከቀረቡት ስትራቴጂዎች መካከል ስታንዳርዳይዝ ሴክቶሪያል የሥራ ምደባ ስትራቴጂ ሰነድ ፣ መሰረታዊና ቴክኒካል የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች ብቃት ስትራቴጂ ሰነድ፣የትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ሰነድ፣የዕሴትና ሥነ-ምግባር ስትራቴጂ ሰነድ ፣የአገልግሎት አቅርቦት ስትራቴጂ ሰነድ እንዲሁም አገራዊ የተገልጋዮች እርካታ የጥናት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

Share this Post