
ዶ/ር መኩሪያ ሀይሌ
የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በአዲስ መንፈስ የተነቃቃ እና አገልጋይነትን የተላበሰ ሲቪል ሰርቫንትን በመፍጠር በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ስርዓትን ለመቀየር ተግባራዊ እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡
ኮሚሽኑ ቀጣይነት ባለው መልኩ የሲቪል ሰርቪስ ስርዓቱን ለመቀየር የሚያስችሉ ተግባራትን በማከናወን ውጤታማ መሆን ይጠበቅበታል፡፡
ለዚህም ቀልጣፋ የተቋማት አደረጃጀት እና የስራ ምዘና ስርዓት መዘርጋት፣ የሰው ሀብት ብቃት ስራ አመራር ስርዓትን መተግበር እና የአፈፃፀም ስራ አመራር ስርዓትን መተግበር ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራቸው ተግባራት ይሆናሉ፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያን በመተግበር ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት እንዲኖር ማድረግና የኤሊክትሮኒክስ ገቨርንመት (E-Governmnet) ስርዓትን መዘርጋት ይጠበቅበታል፡፡
የለውጥ አመራር ስርዓትን በሀገራችን የሲቪል ሰርቪስ ስርዓት ግንባታ ቀጣይነት የሚያረጋግጥና ህሊናዊና ተጨባጭ ነባራዊ ሁኔታ በሚያጣጥም መልኩ ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራባቸው ጉዳዮች ይሆናሉ፡፡
ለሀገራችን ኢትዮጵያ መለወጥ ብሎም እንደ ዘርፍ ለሲቪል ሰርቨሱ ስርዓት መቀየር የሁላችንም ርብርብ እና ሚና ወሳኝ መሆኑ ገልጽ ነው፡፡ ለዚህም በተባበርና በአንድ መንፈስ የሲቪል ሰርቪሱን ስርዓት ለመለወጥ እንድንተጋ ጥሪዮን አቀርባለሁ፡፡
መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር)
የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር

ዜና


“የሴቶች ተጠቃሚነት የሁሉም አጀንዳ ሊሆን ይገባል” ወ/ሮ ስመኝ ውቤ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ምክትል ኮሚሽነር

የሲቪል ሰርቪስ ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጣቸው ጥራት በገለልተኛ አካል ሊመዘን እንደሚገባ ተጠቆመ

ልዩ ነን እና ልዩ ስኬል የሚባል ጉዳይ በአዲሱ የሲቪል ሰርቪስ ስርዓት ቦታ የለውም”
Follow the User Guide to start building your site. Subscribe to